ፈልግ

2024.05.08 Giovani Imprenditori

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡- ፍልሰት የስነ ሕዝብ ቁጥር ማሽቆልቆል ወሳኝ መድኃኒት ነው አሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለሁሉም የዓለማችን ሕዝቦች ለፍትሃዊ፣ ጤናማ እና ክብር ያለው ሥራ አዲስ የተግባር አደረጃጀት አስፈላጊነት ላይ ንግግር በማድረግና ስደተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ጥሩ ፖሊሲዎች አስፈላጊነትን ላይ አጉልተው መናገራቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ረቡዕ ሚያዝያ 30/2016 ዓ.ም ማለዳ ላይ የተቀናጀ የሰው ሐብት ልማት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት የተዘጋጀውን የምክክር መድረክ ተሳታፊዎችን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር በሁሉም ዘርፍ እና በሁሉም ሠራተኞች የተከበረ እና ጨዋ የሆነ ሥራ መስክ የማረጋገጥ አስፈላጊነት ላይ ያተኮረ ንግግር አድርገዋል።

በቫቲካን የባለሙያዎች ምክክር የተከበረ ሥራ ይጠይቃል

ለፕሮጀክቱ አድናቆታቸውን በመግለጽ "የወደፊት ሥራ: ከላውዳቶ ሲ (ውዳሴ ለአንተ ይሁን) በኋላ የጉልበት ሥራ" በሚል መሪ ቃል የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት ተወካዮች፣ የተለያዩ የጳጳሳት ጉባሄዎች እና የገዳማዊያን ማሕበራት ተወካዮች የካቶሊክ እና ሌሎች ቤተ እምነቶች ድርጅቶች፣ የሰራተኛ ማህበራት እና ሌሎች መሰረታዊ ቡድኖችን ጨምሮ ሁሉንም በምክክር ጉባሄው ላይ የተሳተፉትን እንኳን ደህና መጣችሁ ማለታቸው ተገልጿል።

እንክብካቤ ስራ ነው ስራም እንክብካቤ ነው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ባለፉት ስድስት ዓመታት ውስጥ "ለሰዎች ሁሉ ፍትሃዊ፣ ጤናማ እና ክብር ያለው ሥራ" አዳዲስ የተግባር ሞዴሎችን በማውጣታቸው አመስግነው ወደ ሁለተኛው የፕሮጀክቱ ምዕራፍ እንዲሸጋገሩ በማበረታታት በስብሰባው "እንክብካቤ ሥራ ነው፣ ሥራ እንክብካቤ ነው” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የምክክር ጉባሄ ዓለም አቀፍ የለውጥ ማህበረሰብ ለመገንባት እቅድ ያለው ተነሳሽነት ነው ብለዋል።

"ስለምንቀሳቀስበት ማህበራዊ አውድ በቂ ትርጓሜ ለመሞከር ሁሉንም ግላዊ እና ተቋማዊ ሀብቶቻችንን በአንድ ላይ ማሰባሰብ እና እምቅ ችሎታውን ለማወቅ መፈለግ እና በተመሳሳይ ጊዜ እነዚያን ማህበራዊ መቅሰፍት የሆኑ የስርዓት በሽታዎች አስቀድሞ ማወቅ ያስፈልጋል” ብሏል።

የተከበረ ሥራ እና የማዕድን ኢንዱስትሪዎች

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ንግግራቸውን በመቀጠል የሥራ ቡድኑ የለያቸውን አምስት ጉዳዮች፣ ከክብር ሥራና ከማዕድን ኢንዱስትሪዎች ጀምሮ በማንበብ አንስተዋል።

“በኢንዱስትሪ የበለጸገውን ሰሜናዊ ገበያን ለማርካት ብቻ የተወሰኑ ጥሬ ዕቃዎችን ወደ ውጭ መላክ ያለ ክስተት ምንም ዓይነት ውጤት እንዳላስገኘ፣ አንዳንዶቹ በጣም ከባድ ናቸው ፣ በማዕድን ማውጫ ውስጥ የሚገኘውን የሜርኩሪ ወይም የሰልፈር ዳይኦክሳይድ ብክለትን ጨምሮ” በማለት ወቅሷል ። “የሥራ ሁኔታዎችን እና የአካባቢን ተፅእኖን በማገናኘት ለተሳተፉት አካላዊ እና አእምሯዊ ጤንነት እና ደህንነታቸው ውሎ አድሮ የሚመጡትን መዘዞችን በትኩረት መከታተል አስፈላጊ ነው” ብሏል።

የተከበረ ሥራ እና የምግብ ዋስትና

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተከበረ ሥራና የምግብ ዋስትና ጉዳይ ላይ በማተኮር በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ የምግብ ዋስትና እጦት የሚሰቃዩ እና አፋጣኝ ዕርዳታ የሚሹ ሰዎችን ሁኔታ በሐዘን ገልጸዋል።

"እንደ ጋዛ እና ሱዳን ያሉ በጦርነት የተመሰቃቀሉ አካባቢዎች የረሃብ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መኖሪያ መሆናቸውን መዘንጋት የለብንም" ብለዋል ። "ከኢኮኖሚ ውጣ ውረዶች ጋር፣ ተጨማሪ ጠቃሚ የምግብ ዋስትና እጦት መንስኤዎች፣ እነሱም በተራው እንደ ድህነት ካሉ መዋቅራዊ ድክመቶች፣ በምግብ ምርቶች ላይ ከፍተኛ ጥገኛ እና ደካማ መሠረተ ልማት ጋር የተገናኙ ናቸው” ብለዋል።

የተከበረ ስራ እና ስደት

በተከበረ ሥራና በስደት መካከል ያለውን ግንኙነት የተመለከተውን ሦስተኛውን ጉዳይ በመመልከት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደተናገሩት “ብዙ ሰዎች ሥራ ፍለጋ የሚሰደዱ ሲሆን ሌሎች ደግሞ የትውልድ አገራቸውን ጥለው ለመሰደድ ስለሚገደዱ ብዙውን ጊዜ በዓመፅና በድህነት ተንከራተዋል” ያሉ ሲሆን “ብዙውን ጊዜ እንደ ችግር እና ኢኮኖሚያዊ ሸክም በሚታዩ” ሰዎች ላይ ምን ያህል ጭፍን ጥላቻ እና ትክክለኛ ያልሆነ ወይም ርዕዮተ ዓለም መረጃ ወደ አሉታዊ አመለካከቶች እንደሚያመራ እና ለአስተናጋጅ ሀገር ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት በሚያበረክቱት ሥራ ላይ አስተዋፅዖ እንደሚያበረክቱ በመግለጽ ቅድመ ፍረጃን” ነቅፈዋል።

"እዚህ ላይ ዝቅተኛ የወሊድ መጠን ላይ አፅንዖት መስጠት እፈልጋለሁ" ብለዋል ስደት ዝቅተኛ የወሊድ መጠን ምክንያት ለሚፈጠረው ችግር ምላሽ ለመስጠት ይረዳል ብለዋል።

የተከበረ ስራ እና ማህበራዊ ፍትህ

ስለዚህ በተከበረ ሥራ እና በማህበራዊ ፍትህ መካከል ያለው ግንኙነት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደ ተናገሩት ከሆነ "በአካባቢያችን እየተከናወነ ያለውን ነገር በግዴለሽነት መቀበል፣ ከተወሰነ ግዴለሽነት ወይም በቀላሉ እኛ ባለንበት ሁኔታ ውስጥ ስለሌለን በቸልታ መቀበል" የሚለውን ስጋት ለማስወገድ አስፈላጊ ትኩረት ነው ያሉ ሲሆን ብዙውን ጊዜ የተወሳሰቡ ጉዳዮችን ቅረጹና ለእነሱ በቂ ምላሽ ያግኙ” ብለዋል።

ይህ ወደ ማህበራዊ ኢ-እኩልነት እና ኢፍትሃዊነት መጨመር ሊያመራ ይችላል "በተጨማሪም የሠራተኛ ግንኙነቶች እና የሰራተኞች መሠረታዊ መብቶች ይሳተፋሉ እና ያ ጥሩ አይደለም! ” ብለዋል።

የተከበረ ሥራ እና ትክክለኛ የስነ-ምህዳር ሽግግር

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጋራ ቤታችን በተለይም ከሚያስፈልጋቸው የኃይል ምንጮች አንፃር ስነ-ምህዳር፣ ታዳሽ ኃይል እና ሥራ ከፍተኛ የሆነ ግንኙነት ሥላላቸው አንዱ አንዱን በማይጎዳበት ሁኔታ ሊከናወን እንደ ሚገባ እና በሁሉም መስክ ለአከባቢ ጥበቃ በማድረግ ምቹ እና ጤናማ ሥነ-ምህዳር ለሚቀጥለው ትውልድ ማስተላለፍ ይኖርብናል ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

08 May 2024, 18:33