ፈልግ

ሮም በስፖርት እና መንፈሳዊነት ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ልታዘጋጅ እንደሆነ ተነገረ ሮም በስፖርት እና መንፈሳዊነት ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ልታዘጋጅ እንደሆነ ተነገረ   (ANSA)

ሮም በስፖርት እና መንፈሳዊነት ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ልታዘጋጅ እንደሆነ ተነገረ

የፓሪሱ ኦሊምፒክ ውድድር ከመካሄዱ በፊት በቫቲካን እና በቅድስት መንበር የፈረንሳይ ኤምባሲ የሚዘጋጀው “ህይወታችንን መስመር ላይ እናድርግ” የሚል መሪ ቃል ባለው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ ለመሳተፍ 200 የሚሆኑ ተሳታፊዎች ከግንቦት 8 እስከ 10 ድረስ በሮም ሊሰበሰቡ ነው ተብሏል።

አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በዘንድሮው ዓመት በፓሪስ በሚካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር ማዕቀፍ ውስጥ የሚካተተው እና በቅድስት መንበር የፈረንሳይ ኤምባሲ እና የቫቲካን የባህል ጽ/ቤት በጋራ ሆነው ከግንቦት 8 እስከ 10 ድረስ የሚካሄደውን ዓለም አቀፍ የስፖርት እና መንፈሳዊ ኮንፈረንስ በማዘጋጀት ላይ ናቸው።

ዝግጅቱ “ህይወታችንን መስመር እናሲዝ” በሚል ርዕስ (“ሜትሬ ላ ቪታ ኢን ጂዮኮ” በጣሊያንኛ) በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን፥ በዝግጅቱ ላይ ፕሮፌሽናሎች፣ አካለ ስንኩላን ተወዳዳሪዎች፣ አማተር አትሌቶች፣ የዓለም አቀፍ የስፖርት አካላት ተወካዮች፣ የስፖርት ክለቦች አስተዳዳሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲ የስፖርት ‘የሥነ ትምህርት’ ‘የማህበራዊ ሳይንስ’ ‘የአንትሮፖሎጂ’ ‘የፍልስፍና’ እና ‘የሥነ-መለኮት’ ተማሪዎች እንዲሁም በዘመናዊው ማህበረሰብ ውስጥ በጣም ከተለመዱ እና ተከታይ ካፈሩት ባህላዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አንዱ የሆነውን መንፈሳዊ አንድምታን የሚያንፀባርቁ የሃዋሪያዊ ሥራ የስፖርት ክፍል ተወካዮችን ያካተተ 200 ያህል ተሳታፊዎች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የስፖርት መንፈሳዊ ገጽታ

ግንቦት 8 ላይ የጉባኤውን የመክፈቻ ሥነ ስርዓት የሚመሩት ብፁዕ ካርዲናል ሆሴ ቶለንቲኖ ሜንዶንሳ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደተገለጸው ስፖርቶች ሁልጊዜ ከሕይወት መንፈሳዊ ገጽታ ጋር ግንኙነት አላቸው ብለዋል።

በቅድስት መንበር የፈረንሳይ አምባሳደር ወ/ሮ ፍሎረንስ ማንጊን በተገኙበት የቅድስት መንበር የባህልና ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ ሰኞ ዕለት ዝግጅቱን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “የስፖርት ታሪክን ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጋር በንፅፅር ብናይ፣ ስፖርት ለክርስቲያኖች ሕይወት መነሳሳትና ምሳሌ የሆነበት፣ ወይም ክርስትና ራሱ ስፖርትን በሰብዓዊ እይታው እንዳበለፀገው ብዙ ጊዜ ታይቷል” በማለት በአጽንዖት ተናግረዋል።

ቤተክርስቲያን እና ስፖርት

በመሆኑም የጉባኤው ተሳታፊዎች አሁን ላይ የሚካሄዱ የተለያዩ የስፖርት ውድድሮች ለምን ተወዳጅ እንደሆኑ ለመረዳት ይሞክራሉ፣ አደጋዎችን ይለያሉ፣ የበለጠ ወንድማማችነትን፣ ታጋሽ እና ፍትሃዊ ማህበረሰብን ለመገንባት ያላቸውን ጠቀሜታ ይገመግማሉ፣ እንዲሁም እግዚአብሔር በስፖርት ውድድር ላይ እራሱን እንዴት እንደሚገለጥ ይገነዘባሉ ተብሏል። የዝግጅቱ ዓላማ ለሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት እንደሆነ የገለጸው መግለጫ፥ “ስፖርት ለቤተክርስቲያን ምን መልዕክት ያስተላልፋል?” እና “ቤተክርስትያን ስለ ስፖርት ምን ትላለች?” ለሚሉት ሁለት ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት እንደሚጥር እና በዚህም ምክንያት የጉባኤው መሪ ቃል እንደተመረጠ ብፁዕ ካርዲናል ሜንዶንሳ ተናግረዋል።

በጉባኤው ላይ የሚነሱ ጭብጦች

በመጀመሪያው የጉባኤው ቀን ማለትም ግንቦት 8 “በቤተክርስቲያን እና በስፖርት” መካከል ያለው ግንኙነት ላይ የከፍተኛ ደረጃ አትሌቶች ምስክርነት የሚሰማበት እንዲሁም ስፖርትን በወንጌል አገልግሎት ወቅት ያሳተፈ እና ወንጌልን ደግሞ በስፖርት አገልግሎት ላይ ያሳተፈውን የሃዋሪያዊ ሥራ ተሞክሮዎችን ተሳታፊዎቹ እርስ በእርስ የሚካፈሉበት ቀን ይሆናል። ሁለተኛው ቀን (ግንቦት 9) በ “ሰው እና ስፖርት” መካከል ባለው ግንኙነት ላይ ያተኩራል የተባለ ሲሆን፥ ከጣሊያን እና ከፈረንሳይ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ከፍተኛ ብቃት ያላቸው የተናጋሪዎች ቡድን ስፖርትን ከትምህርታዊ፣ ፍልስፍናዊ፣ ማህበራዊ እና ሥነ-መለኮታዊ አንፃር በማንሳት ውይይት ያደርጋሉ። የሶስተኛው ቀን (ግንቦት 10) የሲቪል ማህበረሰቡን የስፖርት ማህበራዊ ጠቀሜታ ለማሳየት በአብሮነት የሚደረግ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ (የወንድማማችነት ቅብብል) የሚደረግበት ይበልጥ በተግባር የሚታይበት ቀን ይሆናል ተብሏል።

 

08 May 2024, 09:04